አውራ አምባ፡ ወቅታዊው ኅብረተ ሰብአዊ አንዋንዋር፡፡ ይህ ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ምኞታዊው አውራ አምባ ኅብርተ ሰብን በሚመለከት ተጽፈው የሚገኙትን ልዩ ልዩ ጽሁፎች ፥ ማለትም በተለይ አራት የማስተሬት ምርምሮችንና በተጨማሪም የተለያዩ ዘገባዎችንና ምስክሮችን ያቀነባበረ ነው ። ይህም በ1972 ዓ/ም በጥቂት አርሶ አደሮች የተጠነሰሰውን የአውራ አምባ ኅብርተ ሰብን ታሪካዊ ሂደት ለማብራራት ይረዳል ። በመቀጠል የአውራ አምባን ባህልና ዋና መሠረት የሆኑትን ፡ ማለትም ሀቀኝነት እኩልነት ትብብርና አስተዋይነትን እናቀርባለን ። ከዚያም በኋላ ይህ 400 ነዋሪ ያለው መንደር ኅብርተ ሰቡን በምን አይነት መልኩ እንዳቀናጀ የምናሳየው ፥ ተቋማቱን፡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን፡ ሴቶችና ወንዶች በተለይ በሥራ መስክ ላይ የሚያሳዩትን እኩልነት፡ የጋብቻ ስርአቱን፡ የኅብርተ ሰቡን ትብብርና ለአዛውንቶች የሚሰጠውን ልዩ እንክብካቤ፡ የልጆችን ሥራና ግዴታ፡ የቀብር ሥርአቱንና በኅብረ ሰቡ ውስጥ የሚከሰተውን ችግር አፈታት እየገለጽን ይሆናል ። በመጨረሻም ለኅብርተ ሰቡ አንጋፋ ለሆነው ለትምህርትና ፡ እንዲሁም አካባቢያቸው ከሚገኙት ብኄረ ሰቦች ከባለሥልጣናትም ሆነ ባጠቃላይ ከኢትዮጵያን ጋርና ከውጭ ሀገር ዜጎች ጋር ላላቸው ግንኙነት ልዩ የሆነ ትኩረት እንሰጠዋለን ። በመደምደሚያም ይህ ከፍተኛ ትምህርት የሚሰጥ አኗኗር ፡ በሂደቱ ላይ ሊደርስበት የሚችለውን አንድ አንድ ችግር እንጠቁማለን ።